ቀጥታ፡

በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት ማንችስተር ሲቲ ከሰንደርላንድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው

አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 23/2018 (ኢዜአ)  በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 19 ሳምንት የመጨረሻ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ሰንደርላንድ ከማንችስተር ሲቲ በስታዲየም ኦፍ ላይት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። 

ሰንደርላንድ 28 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ማንችስተር ሲቲ 40 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በዘንድሮው የውድድር ዓመት ወደ ሊጉ ያደገው ሰንደርላንድ ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል።

በጥሩ አቋም የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ወጥነት ያለው ብቃት በሊጉ ላይ እያሳየ ይገኛል።

ውኃ ሰማያዊዎቹ ካሸነፉ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ዝቅ ያደርጋሉ።

ባለሜዳው ሰንደርላንድ ማሸነፍ ከሁለት ተከታታይ የአቻ ውጤቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት መመለስ ያስችለዋል።


 

በሌሎች መርሐ ግብሮች ሊቨርፑል ከሊድስ ዩናይትድ እና ክሪስታል ፓላስ ከፉልሃም በተመሳሳይ ምሽት 2 30 ላይ ይጫወታሉ።


 

ብሬንትፎርድ ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ከምሽቱ አምስት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም