ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ናትናኤል ዳንኤል እና አዲስ ግደይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ረመዳን የሱፍ ለኢትዮጵያ መድን ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ቢኒያም ካሳሁን በ73ኛው ደቂቃ ላይ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
በሊጉ ሶስተኛ ድሉን ያሳካው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ15 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 11ኛ ከፍ አድርጓል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በ13 ነጥብ ከነበረበት 13ኛ ደረጃ ወደ 14ኛ ዝቅ ብሏል።
ዛሬ በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና መቻልን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ጨዋታዎቹን ተከትሎ የ12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ተጠናቋል። የ13ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳል።