ኢትዮጵያ ቡና ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ቡና ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ቡና መቻልን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ናይጄሪያዊው ዲቫይን ዋቹኩዋ በ44ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
ከሶስት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮጵያ ቡና በ15 ነጥብ ደረጃውን ከ15ኛ ወደ 12ኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ አራተኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው መቻል በ20 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።