በተጠባቂው ጨዋታ አርሰናል አስቶንቪላን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ አርሰናል አስቶንቪላን በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናከረ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 21/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል አስቶንቪላን 4 ለ 1 ረቷል።
ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጋብርኤል ማጋሌስ፣ ማርቲን ዙቢሜንዲ፣ሊያንድሮ ትሮሳርድ እና ጋብርኤል ጄሱስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ኦሊ ዋትኪንስ በ30ኛ ዓመት የልደት ቀኑ ብቸኛውን ጎል ለአስቶንቪላ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
አርሰናል በተለይም በሁለተኛው አጋማሽ የወሰደው ብልጫ ጨዋታውን እንዲያሸንፍ አስችሎታል።
በውድድር ዓመቱ 14ኛ ድሉን ያስመዘገበው የሊጉ መሪ አርሰናል ነጥቡን ወደ 45 ከፍ አድርጓል።
ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አምስት ከፍ ማድረግ ችሏል።
ከስምንት የሊግ ተከታታይ ድሎች በኋላ ሽንፈት ያስተናገደው አስቶንቪላ በ39 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላኛው መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ እና ዎልቭስ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ጆሹዋ ዚርክዜ ለዩናይትድ፣ ላዲስላቭ ክሬጅቺ ለዎልቭስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ቼልሲ እና ቦርንማውዝ ሁለት አቻ ተለያይተዋል። ኤንዞ ፈርናንዴዝ በጨዋታ እና ኮል ፓልመር በፍጹም ቅጣት ምት ለቼልሲ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ዴቪድ ብሩክስ እና ጀስቲን ክላይቨርት ለቦርንማውዝ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
በሌሎች ጨዋታዎች ኒውካስትል ዩናይትድ በርንሌይን 3 ለ 1፣ ኤቨርተን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ ዐ አሸንፈዋል።
ዌስትሃም ዩናይትድ እና ብራይተን ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።