ቀጥታ፡

ሴኔጋል እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 21/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አራት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ማምሻውን ተደርገዋል። 

በታንጀር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሴኔጋል ቤኒንን 3ለ 0 አሸንፋለች።

አብዱላዬ ሴክ እና ሃቢቡ ሞሃመዱ ዲያሎ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የሴኔጋሉ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ በ71ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ሴኔጋል በሰባት ነጥብ ከምድቧ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ጥሎ ማለፍ ገብታለች።

ቤኒን በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።


 

በሌላኛው የምድቡ ጨዋታ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቦትስዋናን 3 ለ 0 አሸንፋለች።

በአል መዲና ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጋኤል ካኩታ በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ናትናኤል ምቡኩ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ጋር አገናኝቷል።

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሰባት ነጥብ በሴኔጋል በግብ ክፍያ ተበልጣ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች።

ቦትስዋና ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ በመያዝ ከውድድሩ ተሰናብታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም