ቱኒዚያ ወደ ጥሎ ማለፍ ገብታለች - ኢዜአ አማርኛ
ቱኒዚያ ወደ ጥሎ ማለፍ ገብታለች
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 21/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ማምሻውን ተካሄደዋል።
በራባት ኦሊምፒክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ታንዛንያ እና ቱኒዚያ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ፌይሰል ሳሉም ለታንዛንያ በጨዋታ፣ እስማኤል ጋርቢ በፍጹም ቅጣት ምት ለቱኒዚያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ቱኒዚያ በአራት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ጥሎ ማለፍ ገብታለች።
ታንዛንያ በሁለት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን ምርጥ ሶስተኛ ሆና ለማለፍ የሌሎች ምድቦችን ውጤት ትጠብቃለች።
በዚሁ ምድብ ዛሬ ማምሻውን በፌዝ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ናይጄሪያ ዩጋንዳን 3 ለ 1 አሸንፋለች።
ራፋኤል ኦንዬዲካ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፖል ኦኑቹ ቀሪዋን ጎል ለናይጄሪያ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ሮጀርስ ማቶ ለዩጋንዳ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። የዩጋንዳው ጀማል ሳሊም በ57ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ውጤቱን ተከትሎ አስቀድሞ ጥሎ ማለፍ የገባችው ናይጄሪያ በዘጠኝ ነጥብ ምድቡን በመሪነት አጠናቅቃለች። በአፍሪካ ዋንጫው የምድብ ጨዋታዎችን በሙሉ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።
የምስራቅ አፍሪካዋ ዩጋንዳ በአንድ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዛ ከውድድሩ ተሰናብታለች።