ቀጥታ፡

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ዳግም ተረከበ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 21/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሲዳማ ቡና ሸገር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል። 

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን እና መስፈን ታፈሰ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ከሶስት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ሲዳማ ቡና በ25 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከፋሲል ከነማ ተረክቧል። በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ድሉን አስመዝግቧል።


 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሸገር ከተማ በ12 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል።

ዛሬ በተደረጉ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነጌሌ አርሲ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 ሲረታ ሀድያ ሆሳዕና ሃዋሳ ከተማን እና አዳማ ከተማ ምድረገነት ሽሬን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም