ቀጥታ፡

አዳማ ከተማ ወደ ድል ተመልሷል 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አዳማ ከተማ ምድረገነት ሽሬን 1 ለ 0 አሸንፏል። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢኒያም አይተን በ86ኛው ደቂቃ ቡድኑን አሸናፊ ያደረገችውን የማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።


 

ከሁለት ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው አዳማ ከተማ ደረጃውን በ20 ነጥብ ከስምንተኛ ወደ ስድስተኛ ከፍ አድርጓል። በሊጉ አምስተኛ ድሉን አስመዝግቧል። 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ለአራተኛ ጊዜ የተሸነፈው ምድረገነት ሽሬ በ14 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም