ሀድያ ሆሳዕና በድል ጉዞው ቀጥሏል - ኢዜአ አማርኛ
ሀድያ ሆሳዕና በድል ጉዞው ቀጥሏል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 21/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ሃዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጫላ ተሺታ በ22ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።
በሊጉ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ሀድያ ሆሳዕና በ16 ነጥብ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 9ኛ ከፍ አድርጓል። አጠቃላይ በውድድር ዓመቱ ያስመዘገባቸውን ድሎች ብዛት ወደ አራት አሳድጓል።
በውድድር ዓመቱ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ በ20 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።