ነጌሌ አርሲ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
ነጌሌ አርሲ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 21/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ነጌሌ አርሲ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሀቢብ ከማል፣ ናትናኤል ሰለሞን እና አለኝታ ማርቆስ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
በሊጉ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው ነጌሌ አርሲ በ19 ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ አምስተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ያሸነፋቸው ጨዋታዎች ብዛት አምስት ደርሰዋል።
በአንጻሩ በሊጉ አራተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በ16 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።