ቀጥታ፡

የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ዘመን ተሻጋሪ ግብ ያለው የትውልድ ጥያቄ ነው - ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 21/2018(ኢዜአ)፦ የባህር በር ባለቤትነት ዘመን ተሻጋሪ ግብ ያለው የትውልድ ጥያቄ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ገለጹ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሒዷል።

በስብሰባው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።


 

ኢትዮጵያ ያቀረበችው የባህር በር ጥያቄ ትውልድ ተሻጋሪ ግብ ያለው የትውልድ ጥያቄ እንደሆነም ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጨምሮ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ስራ እያከናወኑ መሆኑን ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ገልጸዋል።

ከመንግስት ምንም አይነት ድጋፍ ሳይደረግላቸው በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች እየታገሉ ላሉ ዜጎች ሚኒስትሩ ምስጋና አቅርበዋል።

በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችም የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት ለማሳካት እያከናወኑት ያለው ተግባር አበረታች እንደሆነም ገልጸዋል።

በቀጣይም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም