የአማራ ክልል የባሕል ፍርድ ቤቶች ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአማራ ክልል የባሕል ፍርድ ቤቶች ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ነው
ባሕርዳር፤ ታህሳስ 21/2018(ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል የባሕል ፍርድ ቤቶች ሥራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የክልሉና የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
በባሕርዳር ከተማ ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚሁ መርሃ-ግብር ሕጋዊ እውቅና የሚሰጣቸውና በክልሉ የሚገኙ የሽምግልና ሥርዓቶች ሥራቸውን በይፋ እንደሚጀምሩ ተመልክቷል።
በመርሃ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ተገኝተዋል።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አለም አንተ አግደው እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች ታድመዋል።