መቀሌ 70 እንደርታ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
መቀሌ 70 እንደርታ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋርተዋል
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 20/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አቤል ያለው በ40ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪ ሆኗል።
በ80ኛው ደቂቃ ተመስገን ተስፋየ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ለመቀሌ 70 እንደርታ አንድ ነጥብ አስገኝታለች።
ጨዋታውን ተከትሎ መቀሌ 70 እንደርታ በስምንት ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ በ18 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዛሬ በተደረጉ የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ወላይታ ድቻ ከአርባምንጭ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከባህር ዳር ከተማ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በተመሳሳይ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።