ቀጥታ፡

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ባህር ዳር ከተማ አቻ ተለያዩ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 20/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ባህር ዳር ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የወልዋሎው ተጫዋች ሱልጣን በርሄ በ34ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። 

ባህር ዳር ከተማ በጨዋታው ላይ ያገኘውን የቁጥር ብልጫ መጠቀም አልቻለም። 

ውጤቱን ተከትሎ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በዘጠኝ ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውሰጥ ይገኛል።

ባህር ዳር ከተማ በ15 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።

በአሁኑ ሰዓት መቀሌ 70 እንደርታ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም