ቀጥታ፡

ሞዛምቢክ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ድሏን አስመዘገበች 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 19/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ስድስት ጨዋታ ሞዛምቢክ ጋቦንን 3 ለ 2 አሸንፋለች።

በአጋዲር ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፋይሰል ባንጋል እና ዲያጎ ካሊላ በጨዋታ፣ ጌኒ ካታሞ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ፒዬር-ኤሜሪክ ኦቦሚያንግ እና አሌክስ ሞስኬቱ-ሙሶንዳ ለጋቦን ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ጨዋታው በርካታ የግብ እድሎች የተፈጠሩበት ሲሆን ተመጣጣኝ እና አዝናኝ ፉክክር ተደርጎበታል።

ውጤቱን ተከትሎ ሞዛምቢክ በምድብ ስድስት የመጀመሪያ ድሏን በማስመዝገብ በሶስት ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።

በአንጻሩ ሁለተኛ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ቦትስዋና ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ምሽት አምስት ሰዓት ኮትዲቯር ከካሜሮን በማራካሽ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም