የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል እየተከበረ ነው
ሐረር/ሐዋሳ፤ ታህሳስ 19/2018 (ኢዜአ)፡-የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በተለይም በቁልቢና በሀዋሳ ብዛት ያላቸው የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ነው።
የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በቁልቢ ገብርኤል ገዳም በደማቅ ስነ ስርዓት እየተከበረ ነው።
በየዓመቱ ታህሳስ 19 በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊው የንግስ በዓል በቁልቢ ገብርኤል ገዳም በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ታጅቦ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በተመሳሳይ ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሀዋሳ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው።
በከተማዋ የበዓሉን ሂደት ሰላማዊነት የሚያስጠብቁና የትራፊክ ፍሰቱን የሚቆጣጠሩ የተቀናጀ የጸጥታ ሀይልና ወጣቶች ስራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ።
በቁልቢና በሀዋሳ እየተከበረ ባለው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል ሥነ ሥርዓት ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎችና ከውጭ አገራት የመጡ ምዕመናንም በክብረ በዓሉ ላይ በውብ ሀገራዊ አልባሳት ደምቀው ተገኝተዋል።