ቀጥታ፡

ናይጄሪያ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 18/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት ጨዋታ ናይጄሪያ ቱኒዚያን 3 ለ 2 አሸንፋለች።

ማምሻውን በፌዝ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቪክቶር ኦሲሜን፣ ዊልፍሬድ ንዲዲ እና አዴሞላ ሉክማን የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ሞንታሳር ታልቢ በጨዋታ እና አሊ አብዲ በፍጹም ቅጣት ምት ለቱኒዚያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ጨዋታው አዝናኝ እና ተመጣጣኝ ፉክክር ተደርጎበታል።

ውጤቱን ተከትሎ ናይጄሪያ በስድስት ነጥብ ግብጽን ተከትሎ ጥሎ ማለፍ የገባች ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች።

የመጀመሪያ ሽንፈቷን ያስተናገደችው ቱኒዚያ በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ዩጋንዳ እና ታንዛንያ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

የምድብ ሶስት የመጨረሻ መርሃ ግብር ማክሰኞ ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ዩጋንዳ ከናይጄሪያ እና ታንዛንያ ከቱኒዚያ ጋር ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም