ቀጥታ፡

በምስራቅ አፍሪካ ደርቢ ዩጋንዳ እና ታንዛንያ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 18/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት መርሃ ግብር ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በአል መዲና ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሳይመን ምሱቫ በ59ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠረው ጎል ታንዛንያን መሪ አድርጓል።

ኡቼ ኢክፒዙ በ80ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፈው ግብ ዩጋንዳ አቻ ሆናለች።

የዩጋንዳው አለን ኦኬሎ በ91ኛው ደቂቃ የሳተው የፍጹም ቅጣት ምት ሀገሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ እንዳታገኝ አድርጓታል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ተደርጎበታል።

ውጤቱን ተከትሎ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ በምድቡ የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል።

በዚሁ ምድብ ናይጄሪያ ከቱኒዚያ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በፌዝ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም