ቀጥታ፡

በተጠባቂው ጨዋታ አስቶንቪላ ቼልሲን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አገኘ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 18/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አስቶንቪላ ከመመራት ተነስቶ ቼልሲን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆአኦ ፔድሮ በ37ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ቼልሲ መሪ ሆኖ ቆይቷል።

ከእረፍት መልስ ኦሊ ዋትኪንስ በ63ኛው እና በ84ኛው ደቂቃ ያስቆጠራቸው ግቦች አስቶንቪላን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አስጨብጧል።

በሊጉ ስምንተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው አስቶንቪላ በ39 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቼልሲ በ29 ነጥብ ከነበረበት አራተኛ ደረጃ ወደ አምስተኛ ዝቅ ብሏል።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አስቶንቪላ ከሊጉ መሪ አርሰናል ማክሰኞ ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በኤምሬትስ ስታዲየም የሚያደርገው ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም