በተጠባቂው ጨዋታ ሴኔጋል እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
በተጠባቂው ጨዋታ ሴኔጋል እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 18/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አራት መርሃ ግብር ሴኔጋል እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በታንጀር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሴድሪክ ባካምቡ በ61ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን መሪ አድርጓል።
ሳዲዮ ማኔ በ69ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፋት ግብ ሴኔጋል አቻ ሆናለች።
የሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ ጠንካራ ፉክክር ተደርጎበታል።
ውጤቱን ተከትሎ ሴኔጋል እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በምድብ አራት በተመሳሳይ አራት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በዚሁ ምድብ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ቤኒን ቦትስዋናን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
በምድቡ የመጨረሻ መርሃ ግብር ማክሰኞ ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ቤኒን ከሴኔጋል እና ቦትስዋና ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ይጫወታሉ።
ጨዋታዎቹ ወደ ጥሎ ማለፍ የሚገቡ ሀገራት የሚለዩባቸው ናቸው።