ቀጥታ፡

አርሰናል የሊጉን መሪነት ዳግም ተረከበ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 18/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ18ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አርሰናል ብራይተንን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማርቲን ኦዴጋርድ እና የብራይተኑ ጆርጂኒዮ ሩተር በራሱ ላይ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ዲያጎ ጎሜዝ ለብራይተን ብቸኛውን ጎል ከመረብ አሳርፏል።

በሊጉ 13ኛ ድሉን ያስመዘገበው አርሰናል በ42 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከማንችስተር ሲቲ ዳግም ተረክቧል።

በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ብራይተን በ24 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።


 

በሌሎች ጨዋታዎች ሊቨርፑል በራያን ግራቨንበርች እና ፍሎሪያን ዊትዝ ግቦች ዎልቭስን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ሳንቲያጎ ቡዌኖ ለዎልቭስ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።

ብሬንትፎርድ ፉልሃምን 4 ለ 1፣ ፉልሃም ዌስትሃምን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ በርንሌይ ከኤቨርተን ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ቼልሲ ከአስቶንቪላ በቪላ ፓርክ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም