ከለውጡ መንግሥት ወዲህ በስፖርቱ ዘርፍ መነቃቃት የፈጠሩ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል - ኢዜአ አማርኛ
ከለውጡ መንግሥት ወዲህ በስፖርቱ ዘርፍ መነቃቃት የፈጠሩ በርካታ ሥራዎች ተከናውነዋል
ሐረር፤ ታኅሣስ 18/2018 (ኢዜአ)፡- ከለውጡ መንግሥት ወዲህ በስፖርቱ ዘርፍ መነቃቃት የፈጠሩ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን የሐረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙራድ አብዲ አስገነዘቡ።
የስፖርት ብልጽግና እውን እንዲሆን የዘርፉ ማንሰራራት ጉዞ በሚል መሪ ሐሳብ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።
በዚሁ ወቅት ኮሚሽነሩ እንዳሉት፤ በስፖርቱ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በሕዝቡ የተቀናጀ ተሳትፎ ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
ከለውጡ ወዲህ በስፖርቱ ዘርፍ መነቃቃት የፈጠሩ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመው፤ መንግሥት ስፖርቱን በበጀት በመደገፍ፣ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራዎችን የማልማት ሥራ ማከናወኑን አስገንዝበዋል።
ስፖርቱን ከቱሪዝም ዘርፍ በማስተሳሰር ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ የማዘውተሪያ ስፍራዎችን የመጠበቅና የማልማት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
በማንሰራራት ላይ የሚገኘውን ስፖርት ሕዝባዊ መሰረት እንዲኖረው በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቃል ያሉት ደግሞ በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ጃፈር ሱፍያን ናቸው።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ የክልሉ መንግሥት ለስፖርት ዘርፍ መጎልበት እያከናወነ ላለው ጥረት አመሥግነዋል።