ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ቡና ዋና መዳረሻ እየሆነች የመጣችው ቻይና

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 18/2018(ኢዜአ)፦ ቻይና የኢትዮጵያን ቡና በብዛት እየገዙ ከሚገኙ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

የኢትዮጵያ ቡና በቻይናውያን ዘንድ ተወዳጅነቱ እየጨመረ መጥቷል።

ቻይና የዛሬ አምስት አመት የኢትዮጵያን ቡና በመግዛት ከነበረችበት 33ኛ ደረጃ በተያዘው አመት ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ ብላለች።

የኢትዮጵያ ቡናን በቻይና ገበያ የበለጠ ለማስተዋወቅ እና ኤክስፖርቱን ለማሳደግ ያለመ ኮንፍረንስ በቻይና ሁናን ግዛት እየተካሄደ ይገኛል።


 

በቻይና ሁናን ግዛት ጁጆ ከተማ በተዘጋጀው ኮንፍረንስ ከ700ሺህ በላይ ሰዎች የኢትዮጵያን ባለ ልዩ ጣዕም ቡና ለማስቀመስ እቅድ ተይዟል።

ቻይና የኢትዮጵያ ቡና ዋና መዳረሻ እየሆነች የመጣች ሲሆን የዛሬ አምስት አመት የኢትዮጵያን ቡና በመግዛት ከነበረችበት 33ኛ ደረጃ በተያዘው አመት ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ ብላለች።

ኮንፍረንሱ ቻይና በኢትዮጵያ ቡና ያላትን ተደራሽነት የበለጠ ለማሳደግና ወደ ቻይና የሚላከውን የቡና መጠን ማሳደግ ያለመ መሆኑን ኢዜአ ከስፍራው ያገኘው ያመለክታል።

ኮንፍረንሱን ያዘጋጀው የኢትዮ ቻይና የወዳጅነት ኮሚቴ የተሰኘ ድርጅት ነው።

የጁጆ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ የቻይና ከፍተኛ አመራሮች በሁነቱ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።


 

በኮንፍረንሱ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ(ዶ/ር)፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር) እና ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ አመራሮች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም ከ 35ሺህ ቶን በላይ ቡና ለቻይና ገበያ ማቅረቧ በመረጃው ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም