ሞሮኮ እና ማሊ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ሞሮኮ እና ማሊ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 17/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አንድ ተጠባቂ ጨዋታ አዘጋጇ ሞሮኮ እና ማሊ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ማምሻውን በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብራሂም ዲያዝ በመጀመሪያ አጋማሽ የባከኑ ደቂቃዎች ላይ በፍጹም ቅጣት ምት ያስቆጠራት ጎል ሞሮኮ መሪ ሆናለች።
የሪያል ማድሪዱ የክንፍ መስመር ተጫዋች ዲያዝ በውድድሩ ላይ ሁለተኛ ግቡን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ከእረፍት መልስ በ64ኛው ደቂቃ ማሊ ያገኘችውን የፍጹም ቅጣት ምት ያሲን ሲናዮኮ ወደ ግብ በመቀየር ማሊን አቻ አድርጓል። ሲናዮኮ በውድድሩ ላይ ሁለተኛ ግቡን አስቆጥሯል።
ጨዋታው አካላዊ ሽኩቻ ያመዘነበት ሲሆን ሞሮኮ በተጋጣሚ ላይ አንጻራዊ ብልጫ ወስዳለች።
ሞሮኮ ከ900 ደቂቃዎች በኋላ ግብ በኋላ ግብ ተቆጥሮባታል።
የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ የፒኤስጂ የቀድሞ የቡድን አጋሩን እና የሞሮኮውን ተጫዋች አሽራፍ ሀኪሚ እና ብሄራዊ ቡድኑን ለመደገፍ በስታዲየም ተገኝቶ ጨዋታውን ተከታትሏል።
የምድብ አንድ መሪ ሞሮኮ ነጥቧን ወደ አራት ከፍ አድርጋለች።
ማሊ ከሁለት ጨዋታ ሁለት ነጥብ በማግኘት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።
በዚህ ምድብ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ዛምቢያ እና ኮሞሮስ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የምድብ አንድ የመጨረሻ ጨዋታዎች ሰኞ ታህሳስ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።
አዘጋጇ ሞሮኮ ከዛምቢያ እና ኮሞሮስ ከማሊ ይጫወታሉ።
ጨዋታዎቹ ወደ ጥሎ ማለፍ የሚገቡ ቡድኖችን ይለያሉ።