ቀጥታ፡

ዛምቢያ እና ኮሞሮስ አቻ ተለያዩ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 17/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አንድ ጨዋታ ዛምቢያ እና ኮሞሮስ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በመሐመድ አምስተኛ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ተደርጎበታል።

የኮሞሮሱ የክንፍ መስመር ተጫዋች ማይዚያኔ ማኦሊዳ በ19ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል በቪዲዮ በታገዘ ዳኝነት (ቫር) ታይቶ ከጨዋታ ውጪ በመሆኑ ተሽሯል።

በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ግብ ያልተቆጠረበት የመጀመሪያው ጨዋታ ሆኗል።

ውጤቱን ተከትሎ ዛምቢያ በሁለት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

ኮሞሮስ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በምድብ አንድ አዘጋጇ ሞሮኮ ከማሊ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም የምታደርገው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም