ቀጥታ፡

ግብጽ በአፍሪካ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ የገባች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች 

አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 17/2018 (ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታ ግብጽ ደቡብ አፍሪካን 1 ለ 0 አሸንፋለች። 

ማምሻውን በአጋዲር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ መሐመድ ሳላህ በ45ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል። 


 

የግብጹ መሐመድ ሃኒ በመጀመሪያው አጋማሽ ማብቂያ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። 

በሁለተኛው አጋማሽ በ10 ተጫዋች የተጫወተችው ግብጽ ውጤቷን አስጠብቃ ወጥታለች። 

ደቡብ አፍሪካ በማራኪ ጨዋታ የታጀበ እንቅስቃሴ ብታደርግም የግብጽን ተከላካይ መስመር ሰብራ መግባት አልቻለችም።


 

ውጤቱን ተከትሎ ግብጽ በስድስት ነጥብ አንድ ጨዋታ እየቀራት ወደ ጥሎ ማለፉ የገባች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች። 

ደቡብ አፍሪካ በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ አንጎላ እና ዚምባቡዌ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም