የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ
ባህር ዳር፤ ታህሳስ 17/2018 (ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ።
የአማራ ክልል ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ላለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምምከር ሲካሄድ ቆይቷል።
በዛሬው እለት ደግሞ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የቀረቡ የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮና ተወያይቶ አጽድቋል።
ለምክር ቤቱ ቀርቦ ከፀደቀላቸው መካከል 4ቱ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዘርፍ አስተባባሪዎች ሲሆኑ 9ኙ ደግሞ የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎች ሲሆኑ በዚህም መሠረት፦
1ኛ, አህመዲን ሙሐመድ (ዶ/ር)፦ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ
2ኛ, ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፦ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ
3ኛ, ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር)፦ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ
4ኛ, አማኑኤል ፈረደ (ዶ/ር) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የአሥተዳደር ዘርፍ አሥተባባሪ
5ኛ, መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
6ኛ, አቶ ደረጀ ማንደፍሮ ፦ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ
7ኛ, አቶ ጥላሁን ወርቅነህ፦ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
8ኛ, ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ
9ኛ, ኢንጅነር ዳኝነት ፈንታ (ዶ/ር)፦ የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጅ ቢሮ ኃላፊ
10ኛ, አቶ አታላይ ጥላሁን፦ የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ
11ኛ, ጋሻው ሙጨ (ዶ/ር) የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
12ኛ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ
13ኛ, አቶ ዓባይ መንግሥቴ፦ የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሹመታቸው በምክር ቤቱ ጸድቋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት በአቶ አለምአንተ አግደው የቀረቡ 174 የወረዳ ዳኞችን ሹመትም ተቀብሎ አፅድቋል።
በአጠቃላይ ተሿሚዎቹ በአመራር ብቃታቸው፣ በትምህርት ዝግጅታቸው፣ የካበተ የስራ ልምዳቸውና በስነ-ምግባራቸው የተመሰገኑና የክልሉን ሰላም፣ ዕድገትና ልማት ወደፊት ለማሻገር ተግተው ይሰራሉ ተብሎ እምነት የተጣለባቸው እንደሆኑም ተገልጿል።