ቀጥታ፡

አንጎላ እና ዚምባቡዌ ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 17/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ  የምድብ ሁለት ጨዋታ አንጎላ እና ዚምባቡዌ አንድ አቻ ተለያይተዋል። 

በማራካሽ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጌልሰን ዳላ በ24ኛው ደቂቃ አንጎላን መሪ ያደረገችውን ጎል አስቆጥሯል። 

የመጀመሪያ አጋማሽ የባከኑ ደቂቃዎች ላይ ኖውሌጅ ሙሶና ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ዚምባቡዌን አቻ አድርጓል። ለግቧ መቆጠር የአንጎላ ተከላካዮች ድክመት ትልቅ ድርሻ ይወስዳል።

ጨዋታው አዝናኝ እና ጠንካራ ፉክክር ተደርጎበታል። 


 

ውጤቱን ተከትሎ አንጎላ እና ዚምባቡዌ በምድብ ሁለት የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል።

በዚሁ ምድብ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ግብጽ ከደቡብ አፍሪካ በማራካሽ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም