የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድሬዳዋ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ያስገነቧቸውን መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስረከቡ - ኢዜአ አማርኛ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድሬዳዋ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ያስገነቧቸውን መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስረከቡ
ድሬዳዋ፤ ታህሳስ 17/2018(ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድሬዳዋ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ያስገነቧቸውን መኖሪያ ቤቶች አስረክበዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) እና የሚኒስቴሩና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በተገኙበት ዘመናዊ ቤቶቹ ተመርቀው ለባለቤቶቹ የርክክብ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።
ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20 ዘመናዊ ተገጣጣሚ ቤቶችን ያስገነቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር በመተባበር እንደሆነ በመርሃ ግብሩ ተገልጿል።
ከቤቶቹ በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ2 ሚሊየን ብር የተገዙ የተማሪዎች የመማሪያ ቁሶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ቤተሰብ ተማሪዎች አበርክቷል።