ቀጥታ፡

ዕዙ የሕግ የበላይነትን በማስከበር ግዳጁን በላቀ ብቃት እየፈፀመ ይገኛል - ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ

ወልዲያ፤ ታህሳስ 16/2018(ኢዜአ)፦ በመከላከያ ሰራዊት 11ኛው ዕዝ የሀገርን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ ግዳጁን በላቀ በቃት እየፈፀመ መሆኑን የዕዙ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ ገለጹ።

ዕዙ ለሬጅመንትና የሻምበል አመራሮች ያዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና በተጠናቀቀበት ወቅት ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ  እንዳመለከቱት፤  ዕዙ  በተሰማራባቸው ግዳጆች ሁሉ የሕግ የበላይነትንና ሰላምን በማስከበር አበረታች ውጤቶችን  አስገኝቷል።


 

የታሪካዊ ጠላቶችን ተልዕኮ በመቀበል የሚንቀሳቀሰውን ባንዳ ሰራዊቱ ተከታትሎ እርምጃ በመውሰድ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ዕዙ የሕግ የበላይነትን በማስከበር ግዳጁን በላቀ ብቃት እየተወጣ መሆኑን አንስተው በቀጣይም አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።


 

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ንጉስ ዝናቡ፤ የመከላከያ ሰራዊት በከተማዋና አካባቢው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የከተማዋ ህዝብና አስተዳደሩም ከመከላከያ ሰራዊቱ ጎን በመሰለፍ ዘላቂ ሰላምን ለማፅናት የድርሻቸንን እየተወጣን እንገኛለን ብለዋል።

የስልጠናው ተሳታፊ አመራሮችም ከስልጠናው ያገኙትን ተደማሪ አቅም ተጠቅመው ቀጣይ ተልዕኳቸውን በላቀ ብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም