ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ ከመመራት ተነስቶ ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጀሚል ያዕቆብ እና መሐመድ ኑር ናስር የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
አቡበከር አዳሙ ለኢትዮጵያ ቡና ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ ለአራተኛ ጊዜ ያሸነፈው ድሬዳዋ ከተማ በ16 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።
በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በ12 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በአሁኑ ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።