ሃዋሳ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል - ኢዜአ አማርኛ
ሃዋሳ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሃዋሳ ከተማ ሸገር ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ያሬድ ብሩክ እና ጌታነህ ከበደ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ያሬድ መኮንን ለሸገር ከተማ ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በሊጉ ስድስተኛ ድሉን ያስመዘገበው ሃዋሳ ከተማ በ20 ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ያለውን ኢትዮ ኤሌክትሪክ በግብ ክፍያ በልጦ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በውድድር ዓመቱ ለአራተኛ ጊዜ የተሸነፈው ሸገር ከተማ በ12 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።