ተሻሽሎ የቀረበው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂ ለዘላቂ ልማት ጉልህ ፋይዳ አለው - ኢዜአ አማርኛ
ተሻሽሎ የቀረበው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂ ለዘላቂ ልማት ጉልህ ፋይዳ አለው
አርባ ምንጭ፤ ታኅሣስ 16/2018 (ኢዜአ)፡- ተሻሽሎ የቀረበው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂ ለዘላቂ ልማት ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ።
በተሻሻለው የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ስትራቴጂ ላይ ያተኮረ ክልል አቀፍ የባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል።
የደቡብበተሻሻለው የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ስትራቴጂ ላይ ያተኮረ ክልል አቀፍ የባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል። ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አማካሪና የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ማሄ ቦዳ እንዳሉት፤ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ዘመኑን የዋጀ የሥራና የቴክኖሎጂ መፍጠሪያ የማድረግ ተግባር እየተከናወነ ነው።
ተሻሽሎ የቀረበው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂ ለዘላቂ ልማት ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመው፤ ኮሌጆች በክኅሎት የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ገበያው የሚፈልገውን ሥልጠና እንዲሰጡ የሚያበረታታ መሆኑን እና ይህም በመፍጠርና በመፍጠን እሳቤ በመሥራት ስኬት ለማምጣት እንደሚያስችልም አመላክተዋል።
ስትራቴጂው የሰው ኃይል ዕድገትን ከኢኮኖሚ ለውጥ ጋር ለማስተሳሰር ያግዛል ያሉት ደግሞ የክልሉ ሥራና ክኅሎት ቢሮ ምክትልና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ኃላፊ በዛብህ ገበየሁ ናቸው።
በተጨማሪም በትብብር የሚገነባ፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የሚያጠናክር የልኅቀት ማዕከላትን ጥራትና ብቃት ብሎም የሰው ኃይል ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጥ መሆኑን አስረድተዋል።
የወጣቶችን ተስፋ የሚያድስ፣ ሥራ ፈጠራን የሚያበረታታ፣ የሙያ ሥነ-ምግባርን የሚያጎለብት በመሆኑ ከክልሉ የልማት ፀጋዎች ጋር ተጣጥሞ እንደሚሠራም አመላክተዋል።
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የቴክኖሎጂ መፍለቂያ፣ የማምረቻና የኢንዱስትሪ ሥፍራ በማድረግ የክልሉን ዕድገት ለማፋጠን በቅንጅት እንደሚሠራም ጠቁመዋል።