ቀጥታ፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ትናንትን፣ ዛሬን እና ነገን  የሚያስተሳስር የወል ትርክት መገንቢያ መሳሪያ ነው

አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 16/2018 (ኢዜአ)፡-ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ትናንትን፣ ዛሬንና ነገን  የሚያስተሳስር የወል ትርክት መገንቢያ መሳሪያ ነው ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ገለጹ።

"ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት"  በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው ስለ ኢትዮጵያ የውይይት መድረክ ግድቡ በሚገኝበት ጉባ እየተካሄደ ነው። 

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር) ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን ኢትዮጵያውያን በጋራ ተረባርበው እውን ማድረግ ችለዋል ብለዋል። 

ከተደመርን  ምን ያህል ስኬታማ መሆን  እንደሚቻል ግድቡ ታሪካዊ ማሳያ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ህብረ ብሄራዊ አንድነት ይበልጥ እንዲጠናከር አዎንታዊ  አስተዋጽኦ ያበረከተ መሆኑን  አንስተዋል።

ግድቡ  የጋራ ህልምና ተስፋን እውን ያደረገ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰው  ግድቡ ትናንት፣ ዛሬንና ነገን የሚያስተሳስር  ትልቅ  የወል ትርክት መገንቢያ መሳሪያ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ግድቡን በራስ አቅም በመገንባት አፍሪካውያንን በይቻላል መንፈስ ዳግም ለታላቅ ድል ማነሳሳቷን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም