የአማራ ክልል ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የአማራ ክልል ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
ባሕር ዳር፤ ታኅሣስ 16/2018 (ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባዔውን መካሄድ ጀምሯል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለጉባዔው ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።
በውይይቱ በትምህርት አጀማመርና በተከናወኑ ተግባራት ላይ በመምከር የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥም ተጠቁሟል።
እንዲሁም በክልሉ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የፋይናንስ ሕጋዊነትና የክዋኔ ኦዲት ግኝቶችንና የተሰጡ የማሻሻያ ሐሳቦችን የሚያሳይ የተጠቃለለ ሪፖርት ላይ እንደሚመክር ተመላክቷል።
ጉባዔው ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፤ በቆይታው ልዩ ልዩ ዐዋጆች እና ሹመቶችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።