ቀጥታ፡

ኮትዲቯር የአፍሪካ ዋንጫ ክብሯን የማስጠበቅ ጉዞ በድል ጀምራለች

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ስድስት  የመጀመሪያ ጨዋታ ኮትዲቯር ሞዛምቢክን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ማምሻውን በማራካሽ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የማንችስተር ዩናይትዱ የክንፍ ተጫዋች አማድ ዲያሎ በ49ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

የአማካይ ተጫዋቹ ፍራንክ ኬሲ ለዲያሎ ኳሱን አመቻችቶ አቀብሏል።

በጨዋታው ላይ ኮትዲቯር በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እድል በመፍጠር በተጋጣሚዋ ላይ ብልጫ ወስዳለች።

የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ኮትዲቯር የዋንጫ ክብሯን የማስጠበቅ ጉዞ በድል ጀምራለች።

ሞዛምቢክ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃን ይዛለች።

በዚሁ ምድብ ካሜሮን ከጋቦን ምሽት አምስት ላይ በአጋዲር ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም