ቀጥታ፡

ካሜሮን ጋቦንን አሸነፈች 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ስድስት ሁለተኛ ጨዋታ ካሜሮን ጋቦንን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ማምሻውን በአጋዲር ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኤታ ኢዮንግ በስድስተኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቧን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ተመጣጣኝ ፉክክር በተደረገበት ጨዋታ ካሜሮን የተሻሉ የግብ እድሎችን ፈጥራለች።

የአምስት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊናዋ ካሜሮን የመጀመሪያ ሶስት ነጥቧን አግኝታለች።

በዚሁ ምድብ ዛሬ በተካሄደ ጨዋታ ኮትዲቯር ሞዛምቢክን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

በምድቡ ሁለተኛ መርሃ ግብር ኮትዲቯር ከካሜሮን እሁድ ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ጋቦን ከሞዛምቢክ ሌላኛው ጨዋታ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም