ሀድያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ሀድያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው እዮብ አለማየሁ በጨዋታ እና ሄኖክ አርፊጮ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
መልካሙ ቦጋለ ወላይታ ድቻን ከሽንፈት ያልታደገችውን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና በ13 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ወላይታ ድቻ በ10 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ዛሬ በተደረጉ የ11ኛ ሳምንብት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች መቀሌ 70 እንደርታ አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 0፣ ነጌሌ አርሲ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
ባህር ዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።