ቀጥታ፡

ባህር ዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያዩ 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ባህር ዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። 

ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ተደርጓል።

ፋሲል ከነማ በ21 ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ባለው የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ፋሲል ከነማ በሊጉ እስከ አሁን ሽንፈት ያላስተናገደ ቡድን ነው።  

ባህር ዳር ከተማ በ14 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 

በአሁኑ ሰዓት ሀድያ ሆሳዕና ከወላይታ ድቻ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም