ቀጥታ፡

ቡርኪናፋሶ ኢኳቶሪያል ጊኒን አሸነፈች 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አምስት የመጀመሪያ ጨዋታ ቡርኪናፋሶ ኢኳቶሪያል ጊኒን 2 ለ 1 አሸንፋለች። 

በመሐመድ አምስተኛ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ማርቪን አኒቦህ በ85ኛው ደቂቃ በግንባሩ በመግጨት ያስቆጠረው ግብ ኢኳቶሪያል ጊኒን መሪ አድርጓል። 

ጆርጅ ሚኑጉ በ95ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ቡርኪናፋሶ አቻ ሆናለች።

ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ ሲባል 98ኛው ደቂቃ ላይ ኤድመንድ ታፕሶባ ባስቆጠረው ግብ ቡርኪናፋሶ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝታለች። 

የቡርኪናፋሶው አጥቂ ላሲና ትራኦሬ በ71ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ በቪዲዮ በታገዘ ዳኝነት (ቫር) ታይቶ ከጨዋታ ውጪ በመሆኑ ተሽሯል።

የኢኳቶሪያል ጊኒው ተከላካይ ባሲሊዮ ንዶንግ በ50ኘው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ንዶንግ በአፍሪካ ዋንጫው ቀይ ካርድ የተመለከተ የመጀመሪያ ተጫዋች ሆኗል።  


 

ውጤቱን ተከትሎ ቡርኪናፋሶ ምድብ አምስትን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራለች።

በዚሁ ምድብ አልጄሪያ ከሱዳን ምሽት 12 ሰዓት ላይ በፕሪንስ ሙላይ አብደላ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም