መቀሌ 70 እንደርታ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ - ኢዜአ አማርኛ
መቀሌ 70 እንደርታ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሃ ግብር መቀሌ 70 እንደርታ አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብርሃኑ አዳሙ በ15ኛው እና 55ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል።
በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን ያገኘው መቀሌ 70 እንደርታ በስምንት ነጥብ ደረጃውን ከ19 ወደ 18ኛ ከፍ ቢያደርግም አሁንም ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በአንጻሩ በሊጉ ስድስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አርባ ምንጭ ከተማ በአምስት ነጥብ የመጨረሻውን 20ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም።