ቀጥታ፡

ነጌሌ አርሲ ድል ቀንቶታል 

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ነጌሌ አርሲ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል። 

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አሸብር ውሮ በስድስተኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

በሊጉ አራተኛ ድሉን ያስመዘገበው ነጌሌ አርሲ በ16 ነጥብ ደረጃውን ከዘጠነኛ ወደ ሰባተኛ ከፍ አድርጓል። 


 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ሰባተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በስምንት ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም