ቱኒዚያ የአፍሪካ ዋንጫን በድል ጀምራለች - ኢዜአ አማርኛ
ቱኒዚያ የአፍሪካ ዋንጫን በድል ጀምራለች
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት መርሃ ግብር ቱኒዚያ ዩጋንዳን 3 ለ 1 አሸንፋለች።
ትናንት ማምሻውን በራባት ኦሊምፒክ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኤሊያስ አቹሪ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኤሊስ ስኪሪ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ዴኒስ ኦሜዲ ለዩጋንዳ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።
ዩጋንዳ በጨዋታው ላይ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር የነበራት ቢሆንም ቱኒዚያ ኢላማቸውን የጠበቁ ጨዋታዎችን ሙከራ በማድረግ ብልጫ ወስዳለች።
ቱኒዚያ በሶስት ነጥብ ምድቡን መምራት ጀምራለች።
በዚሁ ምድብ በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ ናይጄሪያ ታንዛንያን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
ናይጄሪያ ከቱኒዚያ እና ዩጋንዳ ከታንዛንያ በዚሁ ምድብ የሚደረጉ ቀጣይ ጨዋታዎች ናቸው።