ቀጥታ፡

አርሰናል ለካራባኦ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 15/2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ዋንጫ  የሩብ ፍጻሜ የመጨረሻ መርሃ ግብር አርሰናል ክሪስታል ፓላስን በመለያ ምት አሸንፏል።

ትናንት ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የክሪስታል ፓላሱ ማክሴንስ ላሮክስ በ80ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ባስቆጠረው ጎል አርሰናል መሪ ሆኗል።

ማርክ ጉሂ በ95ኛው ደቂቃ ክሪስታል ፓላስን አቻ ያደረገችውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ጨዋታው ወደ መለያ ምት አምርቷል። በዚህም አርሰናል 8 ለ 7 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ አልፏል።

አርሰናል በግማሽ ፍጻሜው ከቼልሲ ጋር ይጫወታል።

ኒውካስትል ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ ሌላኛው የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር ነው።

የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በጥር ወር 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም