ናይጄሪያ ታንዛንያን አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
ናይጄሪያ ታንዛንያን አሸነፈች
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 14/2018(ኢዜአ)፦ በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሶስት የመጀመሪያ ጨዋታ ናይጄሪያ ታንዛንያን 2 ለ 1 አሸንፋለች።
ማምሻውን በፌስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሴሚ አጃይ በ36ኛው እና አዴሞላ ሉክማን በ52ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ቻርልስ ምሞምባዋ በ50ኛው ደቂቃ ለታንዛንያ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። በጨዋታው ላይ ናይጄሪያ የተሻለ ብልጫ ነበራት።
ውጤቱን ተከትሎ የሶስት ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ናይጄሪያ በሶስት ነጥብ ምድብ ሶስትን መምራት ጀምራለች።
በዚሁ ምድብ ቱኒዚያ ከዩጋንዳ ምሽት አምስት ላይ በራባት ኦሊምፒክ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።