ቀጥታ፡

ኢትዮጵያና አሜሪካ በጤናው ዘርፍ በአጋርነት መሥራት የሚያስችል የ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 14/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና አሜሪካ በጤናው ዘርፍ በአጋርነት መስራት የሚያስችላቸውን የ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

የትብብር ስምምነቱ በዘላቂ ልማት፣ በጋራ ኢንቨስትመንትና የጤና ስርዓትን በማጠናከር ላይ ያተኮረ የኢትዮ-አሜሪካ አዲስ የጤና አጋርነት ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል።


 

የትብብር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ፈርመውታል።

የኢትዮጵያና የአሜሪካ የጤና የአጋርነት ስምምነት ለአምስት ዓመታት የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም