የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ - ኢዜአ አማርኛ
የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ
አዲስ አበባ ፤ታህሳስ 14/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የአቶ አብዱራህማን ሩቤ ሥርዓተ ቀብር በኮልፌ የሙስሊም መካነ መቃብር ተፈፅሟል።
አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ40 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አቶ አብዱራህማን በኢቢሲ እና በኦቢኤን ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉ ሲሆን ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስም የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነበር፡፡
አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱራህማን ሩቤ ኅልፈት የተሰማውን ኀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል።