የአቶ አብዱራህማን ሩቤ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ይፈፀማል - ኢዜአ አማርኛ
የአቶ አብዱራህማን ሩቤ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ይፈፀማል
አዲስ አበባ፤ታህሳስ 14/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ አብዱራህማን ሩቤ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት በኮልፌ የሙስሊም መካነ መቃብር ይፈፀማል።
አቶ አብዱራህማን ሩቤ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አቶ አብዱራህማን ከሪፖርተርነት እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ያገለገሉ ሲሆን፤ በተለይም በኦቢኤን እና በኢቢሲ ከሪፖርተርነት ጀምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡
ከመስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስከአለፈበት ቀን ድረስ ደግሞ የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነበር፡፡
ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት የነበሩት አቶ አብዱራህማን ሩቤ በመልካም ስብዕናቸው እና በስራ ትጋታቸው ምስጉን ነበሩ፡፡
የአቶ አብዱራህማን ሩቤ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት በኮልፌ የሙስሊም መካነ መቃብር ይፈፀማል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱራህማን ሩቤ ህልፈት የተሰማውን ኃዘን በድጋሚ እየገለፀ፤ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል::