የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብዱራህማን ሩቤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ ፤ታህሳስ 14/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ የነበሩት አቶ አብዱራህማን ሩቤ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል::
ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የአቶ አብዱራህማን ሥርዓተ ቀብር ዛሬ እንደሚፈጸም ተገልጿል።
አቶ አብዱራህማን ከሪፖርተርነት እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት አገልግለዋል::
በተለይም በኦቢኤን እና በኢቢሲ ከሪፖርተርነት ጀምሮ በኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል::
ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ ደግሞ የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ ነበር::
አቶ አብዱራህማን ባለትዳር እና የሦስት ልጆች አባት ነበሩ::
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብዱራህማን ሩቤ ህልፈት የተሰማውን ሃዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጆቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል::