ቀጥታ፡

በሴቶች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሸገር ከተማ ተስተካካይ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 14/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሸገር ከተማ ጨዋታቸውን ያከናውናለሉ

ጨዋታው በአበበ ቢቂላ መታሰቢያ ስታዲየም ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ይካሄዳል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሊጉ እስከ አሁን ባደረጋቸው 11 ጨዋታዎች ስምንቱን ሲያሸንፍ አንድ ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል።

በጨዋታዎቹ ላይ 27 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ ሁለት ጎሎች ተቆጥረውበታል።

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ26 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚው ሸገር ከተማ በሊጉ 12 ጨዋታዎችን አድርጎ ዘጠኙን ሲያሸንፍ በሶስቱ ተሸንፏል። 20 ጎሎችን ሲያስቆጥር 11 ግቦች ተቆጥረውበታል።

አዲስ አዳጊው ሸገር ከተማ በ27 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በጠንካራ አቋም ላይ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የቡድኖቹ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ በነበረው ተሳትፎ ምክንያት የተራዘመ ነው።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀሪ ተስተካካይ መርሃ ግብሩን ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከሲዳማ ቡና ጋር እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ከተስተካካይ መርሃ ግብሮች ውጪ መጠናቀቁ ይታወቃል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ36 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው።

አርባ ምንጭ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ 13ኛ እና 14ኛ ደረጃን ይዘው ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም